ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሠላማዊ በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛል

Share this story

Posted on: Dec 20,2018

በአለፉት ሦስት ቀናት በተወሰነ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የመማር ማስተማሩ ስራ እንደተስተጓጎለ ይታወቃል፡፡ በእዚህ ላይ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ከአካባቢው ማህበረሰብና ከተማሪ ተወካዮች ጋር የተለያዩ ውይይቶች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ ዩኒቨርሲቲውም በተማሪዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ያለው የተማሪዎቻችንን ሠላምና ደህንነት ማስጠበቅ ላይ ነው፡፡ በእዚህም ምክንያት ተማሪዎቻችን እንደሰጋት የሚያነሷቸውን የደህንነት ጥያቄዎች አስተማማኝ ለማድረግ ተጨማሪ የፌዴራል ኃይል በመጨመር የግቢው ጥበቃ የተጠናከረ እና አስተማማኝ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

በነገው እለት የጋራ መስማማት ላይ ለመድረስና ትምህርት ለማስጀመር ከግቢ ከወጡ ተማሪዎች ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡ በእዚሁ አጋጣሚ ሁሉም ሊረዳ የሚገበው የዩኒቨርሲቲው ፀጥታ ፍፁም አስተማማኝ መሆኑን ነው፡፡